Your cart is currently empty!
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 08, 2026)
1ኛ ዙር የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡– አ/ከ/ክ/ከ/ወረዳ 12 ፋይናንስ ግዢ ዋ/ስ/ሂ/የጨ/ቁ 002/2018
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት 2ኛ ዙር ለሚያከናውነው አጠቃላይ የአላቂ እቃ እንዲሁም አገልግሎት ግዥ የዝግጅት ምእራፉን አጠናቆ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የእቃና አገልግሎት ግዥ መደቦች ላይ ተቋሙ ያስቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል።
- ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያና አላቂ እቃዎች………………………..CPO (2%)
- ሎት 2 የፅዳት እቃዎች………………………CPO (2%)
- ሎት 3. የደንብ ልብስ……………………….CPO (2%)
- ሎት 4 ቋሚ እቃዎች……………………….CPO (2%)
- ሎት 5.የህትመት ስራዎች………………………….. CPO 5000.00 ብር
- ሎት 6.የግብርና ግብአት እቃዎች……………………………. CPO 5000.00 ብር
መስሪያ ቤታችን ከላይ በተገለፀው የግዥ መደብ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ወይም አቅራቢን አወዳድሮ ግዥውን ለመፈፀም ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
2. የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
3. የዘመኑን ግብር የከፈለበት ክሊራንስና ህጋዊ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
4. የጨረታ ሰነዱ ሙሉ እያንዳንዱ ገፅ ተሞልቶ ተፈርሞ ማህተም ተደርጎበት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መመለስ አለበት ይህን ሳያደርግ የጨረታ ሰነዱን ለሚመልስ ነጋዴ ከጨረታው ውድድር ውጪ እንደሚሆኑ እናሳውቃለን)።
ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ኮልፌ አጠና ተራ መናፈሻ ፊት ለፊት የተቋሙ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በሚገኘው ፋይናንስ ፅ/ቤት በግንባር በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 ብር (ለአንድ ሎት) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል ከላይ በተገለፀው መሰረት ከሎት 1-4 የሚያቀርቡትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% እንዲሁም ከሎት 5-6 ደግሞ 5000.00 /አምስት ሺ ብር/ ህጋዊ CPO በተቋማችን ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከመዋዋላቸው በፊት ያሸነፉትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በድርጅታችን ስም ህጋዊ CPO በማሰራት ለጨረታ ውል ማስከበሪያነት ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን ሙሉውን በታሸገ ፖስታ ኦሪጅናልና ኮፒ ብለው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጫራች የሚሞላውን ክፍል በጠቅላላ ሞልተው ፈርመው ማህተም አድርገው የጨረታ መቀበያ ቀነ ገደቡ ሳያልፍ ለዚሁ ስራ ተብሎ በፅ/ቤቱ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት የመጠቀሚያ ግዜው ቢያንስ 1 አመትና ከዛ በላይ የሆነ እና በሳምፕሉ መሰረት አድርገው ወረዳው ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለጥቃቅንና አንስተኛ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበርያ አስተያየት የምናደርገው ለሚያመርቱት ምርት ብቻ እሱንም በደብዳቤ የምናስተናግድ መሆኑ እንገልፃለን። ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰአት ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ፡-
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም እረፍት ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።
አድራሻ፡-
ኮልፌ አጠና ተራ ኮልፌ ፓርክ ፈት ለፊት ወይም ቁጠባ ሰፈር ጀርባ ወደ ፊሊጶስ ቤተክርስቲያን/ሎሚ ሜዳ በሚወስደው መንገድ 200ሜ ወደ ግራ ገባ ብሎ ለበለጠ መረጃ በ0118278077/0910584301 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተአ ወረዳ 12 ፋይናንስ ፅ/ቤት