Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የጋራ መኖሪያ ቤት እንዲሁም አውቶ ሞቢል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪው የብድር ዕዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል
Reporter(Feb 08, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በብድር የሰጠ ገንዘብ በብድር ውሉ መሰረት ስላልተከፈለ ባንኩ በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድሩ መከፈል ዋስትና መያዣ እንዲሆን ሥልጣን ባለው አካል በማስመዝገብ ያሳገደውን ንብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪው የብድር ዕዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል:: ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ሐራጁ በሚካሄድበት ዕለት ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ በመገኘት በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዟል።
ሠንጠረዥ ሀ
|
የተበዳሪው ስም
|
የንብረት አስያዥ ስም
|
የንብረት ዓይነት
|
አበዳሪ ቅርንጫፍ
|
ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ |
የካርታ ቁጥር
|
የቦታ ስፋት
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ |
||
|
ክልል/ ከተማ |
ዞን/ ክ/ከተማ |
ወረዳ/ ቀበሌ |
||||||||
|
አቶ ወርቁ ለማ ሁንዴ
|
አቶ ወርቁ ለማ ሁንዴ
|
የጋራ መኖሪያ ቤት
|
አርሰዲ
|
ኦሮሚያ
|
ቢሾፍቱ
|
ዲባዩ
|
WLEN/3-0159-A18 B/M2/B10/1st/R10/4
|
61.86 ከ.ሜ
|
2,238,394.26
|
ጨረታው መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት ከ4፡00-6፡00 በባንኩ ሆረ አርሰዲ ቅርንጫፍ ይካሄዳል |
ሠንጠረዥ ለ
|
የተበዳሪው ስም
|
የንብረት አስያዥ ስም
|
የተሽከርካሪ ዓይነት
|
አበዳሪው ቅርንጫፍ
|
የተሸከርካሪው መለያ ቁጥሮች |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን፤ ቦታ እና ሰዓት |
|||
|
የሰሌዳ ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር
|
የሞቶር ቁ.
|
ሞደል
|
||||||
|
አቶ ሙሀመድሳለህ ከሊል አብዱልባቂ
|
አቶ ከሊል አብዱልባቂ
|
አውቶ ሞቢል
|
አበበች ጎበና
|
አአ-02-B29301
|
SJNFEAJ11 UZ003365
|
HRA2- 438006A
|
FEAJ11
|
1,750,000
|
ጨረታው የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት ከ4፡00-6፡00 ፍላሚንጎ ባንኩ አጠገብ ታወር በተከራየዉ ጌት ሃዉስ ህንጻ 3ኛ ፎቅ አዳራሽ ዉስጥ ይካሄዳል |
ተጫራቾች እንዲያውቋቸው
1. ተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4(25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ስም አሰርተው ይዞ በአድራሻ ቀርበው በመመዝገብ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ:: ጨረታውን በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ፣ ንግድ ፈቃድና የድርጅቱን ውክልና እና የታደሰ መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት::
2. ጨረታው ከላይ ቀንና ሰዓቱ በተገለፀው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይካሄዳል፤ ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ግን ሐራጁ እነሱ በሌሉበት ቦታ ይካሄዳል.
3. ንብረቶቹ በሥራ ሰዓት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለሠንጠረዥ ሀ በስልክ ቁጥር 0911369162 ወይም 0913842134; ለሠንጠረዥ ለ በስልክ ቁጥር 0912201482 ወይም 0992685141 ደዉለው በመጠየቅ ንብረቶቹን መጎብኘት ይቻላል::
4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15(አሥራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ እንዲቀርብ ይደረጋል:: በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል::
5. የጨረታው አሸናፊ በሕጉ መሠረት ለመንግስት የሚከፈለውን ማንኛውንም የቫትና ታክስ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን ከፍሎ ስሙ ወደ እራሱ እንዲዛወር ያደርገል::
6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::