ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ለሲቪል፣ ለሳኒተሪ እና ለኤሌክትሪክ ስራዎች የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ የግንባታ ግብአቶች (ዕቃዎች) እና የአልሙኒየም ስራዎች (አቅርቦትና ተከላ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 10, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሠነድ ቁጥር – ልዲቁኮ – 08/2018

ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን በግቢው ውስጥ ለሚያስገነባው G+2+ T የዲዛይን ህንፃ ጥቅም ላይ የሚውል ማለትም፡-

  • ለሲቪል፣ ለሳኒተሪ እና ለኤሌክትሪክ ስራዎች የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ የግንባታ ግብአቶች(ዕቃዎች) እና
  • የአልሙኒየም ስራዎች (አቅርቦትና ተከላ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላል።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የዘመኑን የግብር ግዴታ ስለመወጣታቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህር ዳር የግዥ የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 007 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል።

3. ጨረታው የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ለመገኘት የቻሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ ወይም እንደተጠየቀ ወዲያውኑ በሚከፈል የባንክ ጋራንቲ በፖስታ አሽገው እስከጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 007 ማቅረብ ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

5. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 058-218-0638 ሞባይል 09-96-14-20-56 በመደወል
ወይም በፋክስ ቁጥር 058-218-0550 በመላክ መጠየቅ ይቻላል።

ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *