በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውል የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 11, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውል የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ደብረ ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 /አምሰት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ/CPO/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ባሸነፈባቸው የዕቃ ዝርዝር መሰረት ከመ/ቤቱ ጋር የውል ስምምነት መፈራረም ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች እቃዎቹን ከነ ትራንስፖርት ወጪያቸው የሚሸጡበትን ዋጋና አይነት በመለየት በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ሞልተው በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት 230-1130 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት ውስጥ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው በ16ኛው ቀን 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተዘግቶ በዚህ ቀን 500 ሰዓት ይከፈታል።16ኛው ቀን ቅዳሜ እሑድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይካሄዳል፡፡ ተጫራቾች በሚፈልጉትና ማቅረብ በሚችሉበት እቃዎች ላይ ብቻ መወዳደር ይችላሉ። ሆኖም ለአንድ ዓይነት እቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም።

6. ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉበትን እቃዎች /ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት የማጓጓዣ፣ የማስጫኛና የማውረጃ ወጪ መቻል ይኖርባቸዋል።

7. /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃ አይነት ወይም ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 09 63 22 61 05 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመደወል ወይም ደ/ሊባኖስ ወረዳ //ቤት እቃ ግዥ ክፍል በግንባር ቀርበው መረዳት ይችላሉ።
  • አድራሻኝ፡ሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ሊባኖስ ወረዳ //ቤት ከአ/ በስተ ሰሜን 89 . ላይ ይገኛ።

በሰሜን ሸዋ ዞን የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ገንዘብ /ቤት