Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ለ2018 በጀት ዓመት ለአካዳሚው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 10, 2026)
ለመጀመሪያ ዙር የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ለ2018 በጀት ዓመት ለአካዳሚው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዥዎችን ቀጥሎ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃዎች/ አቅርቦት ዓይነት |
ሎት |
ጨ/ማስከበሪያ |
የሎት መለያ ቁጥር |
|
|
የጽህፈት ዕቃዎች ግዥ |
01 |
5,000 |
አ/አ/አ/አካ/ግ/ጨ/_003/2018 |
|
|
የጽዳት ዕቃዎች |
02 |
5,000 |
አ/አ/አ/አካ/ግ/ጨ/_003/2018 |
|
|
የIT & Electronics” ዕቃዎች ግዥ |
03 |
5,000 |
አ/አ/አ/አካ/ግ/ጨ/_003/2018 |
|
|
የህትመት አገልግሎት ስራዎች ግዥ |
04 |
5,000 |
አ/አ/አ/አካ/ግ/ጨ/_003/2018 |
|
|
የደንብ ልብስ ግዥ |
05 |
5,000 |
አ/አ/አ/አካ/ግ/ጨ/_003/2018 |
|
|
የኮምፒዉተር፡የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን የጥገና አገልግሎት ግዥ |
06 |
5,000 |
አ/አ/አ/አካ/ግ/ጨ/_003/2018 |
|
|
የህጻናት መቆያ ግብዓቶች ግዥ |
07 |
5,000 |
አ/አ/አ/አካ/ግ/ጨ/_003/2018 |
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዝርዝር መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡–
1. በዘመኑ እና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣ በታክስ ባለስልጣን የተሰጠ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፡ቲን ሰርተፍኬት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ፣ በመንግሥት ግዥ ለመሳተፍ በመንግስት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ኤጄንሲ ድረ–ገፅ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ እንዲሁም የሚጠበቅባቸውን የግብር ግዴታ የተወጡና በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ (ክሊራንስ) ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ከአራት ኪሎ አደባባይ ወደ ፒያሳ በሚስደዉ መንገድ ዳብር ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘዉ የአድስ አበባ አመራር አካዳሚ የግዥ ዳይሬክተር 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በሚገኘው ዘዉተር የስራ ሰዓት በመቅርብ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በቀረበው የብር መጠን መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ “ለአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ” በሚል አድራሻ በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ወይም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸው መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ በሁለት በታሸገ ኤንቬሎፕ (ፖስታ) ማለትም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በሚል የሚያቀርቡ ሲሆን በአንደኛው ቴክኒካል ኤንቬሎፕ (ፖስታ) ላይ ንግድ ፍቃድ፣ ንግድ ምዝገባ፣ ቲን ስተፍኬት፣ ቫት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ፣ ክሊራንስ እና CPO) በአንድ ላይ በሁለተኛው ፋይናንሻል ኤንቬሎፕ (ፖስታ) የመወዳደሪያ ዋጋችሁን ብቻ በመሙላት እና የሁለቱንም ኦርጅናል ሰነዶች አንድ አንድ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቹዋል። ተጫራቹ ከአካዳሚዉ የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ የተጠየቁትን ሞልተዉ እያንዳንዱ ግጽ ላይ ህተም በምምታት ፖስታዉን አሸጋችሁ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች በፖስታቸው ላይ የድርጅታቸውን ስም በመፃፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በመጽሀፍ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት አለባቸው።
5. ከሎት 1-7ለ ለቀረቡት የጨረታ መክፈቻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. የጨረታ ሰነድ መክፈቻ ቀን ላይ ህዝባዊ ባአል (ካላንደር የሚዘጋ) ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
7. አካዳሚው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ስለ ጨረታው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ቀጥሎ ባለው የስልክ ቁጥር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ስልክ ቁጥር 0116- 67-33-90
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ