Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል
Addis Zemen(Feb 10, 2026)
የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-SSNT-T599
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሰባት (7) የክልል አየር ማረፊያዎች የሚገኙ 22 (ሃያ ሁለት) ክፍት ቦታዎችን ለአስር (10) አይነት አገልግሎቶች ((አርባ ምንጭ (ካፌቴሪያ እና የመረጃ ዴስክ)፣ አሶሳ (የመኪና ማቆሚያ፣ የመታሰቢያ ቁሳቁስ ሱቅ እና የመረጃ ዴስክ)፣ ሀዋሳ (ሚኒማርኬት ሱቅ፣ የባህል አልባሳት ፣ የጌጣጌጥ ሱቅ እና የመረጃ ዴስክ)፣ ጂንካ (የመታሰቢያ ቁሳቁስ ሱቅ እና የመረጃ ዴስክ)፣ ጋምቤላ (የመኪና ማቆሚያ እና ካፌ እና ሬስቶራንት)፣ የጎባ ሮቤ (ካፌ እና ሬስቶራንት፣ የባህል ቡና እና የሻንጣ መጠቅለያ) እና ጂማ (ሚኒማርኬት ሱቅ እና የመረጃ ዴስክ)) ለማቅረብ ፈቃደኛ ለሆኑ ብቁ የአገልግሎት አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡–
1. ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው ማንኛውም ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT T599 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
3 በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት እያንዳንዱ ጨረታ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ9ዐ ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በታሸገ እና በተለየ ኤንቨሎፕ እና “የጨረታ ዋስትና የሚል ጽሑፍ የተደረገበትን የጨረታ ቦንድ የያዘ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት። ከኢንሹራንስ እና ቅደመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
4. ተጫራቾች ህጋዊ ሰነዶቻቸውን (የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የTIN እና የቫት ሰርተፊኬት) እና የመወዳደሪያ ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል ዋናውን በአንድ ኤንቨሎፕ እና ኮፒውን በሌላ ኤንቨሎፕ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንገ ነን ቴክኒካል ከፍል
አሸብር ተሾመ:በስልክ ቁጥር፡ +251-11 517-4918 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
ኢሜል: ashebirte@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።