በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓ.ም በመደበኛ በጀት ለሚያስገነባዉ G+3 ለቢሮ ግንባታ ስራ አገልግሎት  የሚውሉ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓ.ም በመደበኛ በጀት ለሚያስገነባዉ G+3 ለቢሮ ግንባታ ስራ አገልግሎት  የሚውሉ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Apr 06, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓ.ም በመደበኛ በጀት ለሚያስገነባዉ G+3 ለቢሮ ግንባታ ስራ አገልግሎት  የሚውሉ

  • ሎት 1. የዉሃ ዕቃዎችና መገጣጠሚያዎች፣
  • ሎት 2. ኤሌክትሪክ እቃዎች፣
  • ሎት 3. የቢሮ በርና መስኮት እቃዎች እና
  • ሎት 4 የግንባታ ማቴሪያሎች 

ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው፡-

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ተጫራቾች የሚጫረቱት የግዥ የገንዘብ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት  የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው  ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የሚገዙት የእቃ ዓይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ደባርቅ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ  ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ  በመሂ 1 ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ  ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም  ያስያዙት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) ከ2 በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡

8. ማንኛውም ተወዳዳሪ ለሚወዳደሩበት ጨረታ በየሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ ነጣጥለው ማቅረብ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሎ ሥርዝ ድልዝ ካለው በራሳቸው ፊርማ ፓራፍ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ  በደባርቅ ዙርያ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡

10.አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም  በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በማስያዝ ውል መያዝ ይጠበቅበታል፡፡

11. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጋዜጣ እትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡

12. የጨረታ መክፈቻ የመጨረሻ ቀን ጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ሆኖ ይህ ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ህጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡

13.የእቃዉ ርክክብ ቦታ ደባርቅ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡

14.ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡ የጨረታው ውድድር የሚካሄደው  በሎት በድምር ዋጋ ይሆናል፡፡

15.የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

16.መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

17.መስሪያ ቤቱ አሸናፊ ድርጅቱን ውል በሚሰጥበት ጊዜ ከጠቅላላ ዋጋው 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡

18.ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 117 00 11 /09 18 43 91 35 ወይም በፋክስ ቁጥር 058 117 04 21 በመላክ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *