Be'kur (Apr 06, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን Standard Nutrition (SMART) Survey በሰሜን ሽዋ ዞን በሲያደብር ዋዩ እና አንሳሮ ወረዳዎች የመረጃ ማሰባሰብ፣ ትንተናና ሪፖርት ለማዘጋጀት የመስክ መኪና ኪራይ ግዥ (የአገልግሎት ግዥ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት እና የሚገዙ እቃዎች ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተገለጹትን መስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5. የመስክ መኪና ኪራይ ግዥ (የአገልግሎት ግዥ) አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮሚሽኑ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት፡፡
9. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
10.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
12.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13.በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
14.የገዥ መ/ቤት አድራሻ አ.ብ.ክ.መ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባሕር ዳር ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 058 218 00 14 /058 218 11 03 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን