Be'kur (Apr 06, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት፣ በጤና እና በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ከዩኒሴፍ በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ በብቁ ወጣት ፕሮግራም የመረጃ ሶፍትዌር በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በማወዳደር በግልጽ ጨረታ ማስለማት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ባሕር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፁሁፍ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ 9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
7. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ልማት ማህበር