የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም የፕሪንተር ቀለም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም የፕሪንተር ቀለም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 06, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 007

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ 2018 . ክልላዊ ፈተናን አስመልክቶ ሰርተፊኬት ፕሪንት ለማድረግ የሚያገለግል የፕሪንተር ቀለም Type Black Original Laser jet M6l Toner cartridge ቅልጥፍናና አቅም (Capacity)አንዱ እስከ 10,000 ገጾች ፕሪንት ማድረግ አቅም ያለው ጥራት (Quality)እውነተኛ ኦሪጅናል ምርት (1 ደረጃ)(Genuine Product) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ማንኛውም በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይንም መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፣

መስፈርት

1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ አስተማማኝ ዋስትና መስጠት የሚችል፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንዳንድ ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 12,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 800 ሰዓት ታሽጎ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሚያስገቡበት ቀን ናሙና አብሮ ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. /ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 046-771-06-88 መደወል ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ (ወራቤ)


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *