የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት የተለያዩ ዕቃዎችን ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት የተለያዩ ዕቃዎችን ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 07, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 03/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • 1. ሎት 1ደንብ ልብስ የሴት ውስጥ ልብስ ጨርቅ፣ የወንድና የሴት ቦርሳ፤
  • ሎት 2የጽ/መሳሪያዎች፡ ክላሰር ባለ 250 ግራም፣ ማርከርና አቃፊ ባለብረትና የመሳሰሉት፤
  • ሎት 3የፅዳት ዕቃዎች አልኮል ኤርፍሬሽና ሳኒታይዘርና የመሳሰሉት፤
  • ሎት 4ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፡ፍላሽ፣ መቀስና የመሳሰሉት
  • ሎት 5ኤሌክትሮኒክስ፡ስማርት ቲቪ፣ ዘመናዊ የቡና ካፒቺኖ ማኪያቶ ማሽን፤
  • ሎት 6ፈርኒቸር፡ – አትሮኖስ፣ ኮፊ ቴብል፣ ላተራል፤
  • ሎት 7የመኪና ጌጣ ጌጥ እና መለዋወጫዎች፡የመሪ ልብስ፣ የመኪና ማረጋገጫ፣ ክሪክ፣ የተለያዩ የመኪና መፍቻዎችና የመሳሰሉት ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ፣ የቫትና የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ሌሎች ለጨረታ መወዳደር አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎ ማቅርበ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ፡ ሎት 1. የደንብ ልብስ ብር 3000 ሎት 2. የጽ/መሳሪያዎች ለብር 5000 ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች ብር 5,000 ሎት 4. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 3,000 ሎት 5. ኤሌክትሮኒክስ ብር 5000 ሎት 6. ፈርኒቸር ብር 3,000 ሎት 7. የመኪና ጌጣጌጥ እና መለዋወጫዎች ብር 3,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስም አሰርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግሥት /ቤት የዋስትና ደብዳቤ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 359 ሰዓት ድረስ በመውሰድ የመወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮሚሽኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ ዮቤክ ሕንፃ 8 አስ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱን ባስገቡበት የቤክ ሕንፃ 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ግዥ ዳይሬክቶሬት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ በዕለቱ ይከፈታል።

4. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀበት 7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ 6 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት።

5. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደርያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ ምዝገባ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቶችን (የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናልና የተጠየቁ አስፈላጊ የንግድ ፈቃዶችና መረጃዎች ኮፒ) በፖስታ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።

7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለሁ ማለት አይችልም።

8. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ሕጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል።

9. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል።

ማሳሰቢያ፤ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሑድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።

አድራሻ፡ልደታ ክፍለ ከተማ ሜክሲኮ ሠንጋ ተራ የቤክ ሕንፃ 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-5-57-78-46 እና 0913-04-5738 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

ሰነዱን ማሳሰቢያ፡የዋጋ ማቅረቢያውን በራስ ሞልቶ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፤ መሞላት ያለበት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች ዋጋ ኮፒ ተደርጎ በመሙላት ብቻ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቭስትመንት ኮሚሽን