Addis Zemen (Apr 06, 2026)
አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 2367
የኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ድርጅት መኖሪያ ቤቶችን በሀገር ውስጥ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ፕሮጀክቶችን ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የተሟላ የሰው ኃይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚቀጠሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
1. ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ወረቀት ያላቸው ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2018 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ (Supplier list) ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው የሚያስገቡት የቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶች እያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታ ላይ ፊርማ ፣ፕሮጀክት ስምና የድርጅቱ ማህተም በማድረግ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ በማሽግ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ በማሸግ የታሸጉትን ሶስትቴክኒካል ሰነዶች በአንድ ላይ በማሸግ እና ሶስቱን ፋናንሻል ሰነዶች በአንድ ላይ በማሸግ ሁለቱን የታሸጉ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶች በአንድ አይነት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ስም ፣ፊርማ፣ ማህተም እና የሚወዳደሩትን ፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ ካዛንችስ ረድኤት ህንፃ 9ኛ ፎቅ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው(original) እና የማይመለስ ቅጂ (Copy) ይዞ በመቅረብ ሰነዶች መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተቋራጭ እስከ 11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ካሳንችስ ረድኤት ህንፃ 9ኛ ፎቅ ላይ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
4 መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- ጨረታ ሰነድ ለማስገባት የሚቀርቡ ተጫራቾች ህጋዊ መታወቂያ ወይም ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልና እና መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ ካሳንችስ ረድኤት ህንፃ 9ኛ ፎቅ ጥያቄ መቅረብ ይችላሉ።
- አድራሻ፡-ካሳንችስ መናኸሪያ ሆቴል አካባቢ
የኪ ሃውሰንግ ፋይናንስ ሶሉሸን