Be'kur (Apr 06, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የዋርካ ሜዲካል እና ቢዝነስ አክሲዎን ማህበር በሞጣ ከተማ አስተዳደር በተረከበዉ ቦታ 5250 ካሬ ሜትር ላይ ለጄኔራል ጠቅላላ ቲችንግ ሆስፒታል የሚሆን G+0፣ G+4 እና B+G+4 ሌሎች ለቢሮ እና ለተለያዩ ቢዝነስ አገልግሎት ማለትም ለመሰብሰቢያ አዳራሽ ለባንክ ለኢንሹራንስ እና ለሌሎች ቢዝነስ አገልግሎቶች የሚዉሉ ህንፃዎች የተለያዩ ክፍሎች ዲዛይን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው እና የታደሰ የሙያ ፈቃድ የደረጃ 1 እና 2 ያላቸዉ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከዋርካ ሆስፒታል ከረዳት ገ/ያዥ ሰነዱን ብር 1,000 (አንድ ሽህ ብር) በመግዛት ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ጥቅል ዋጋ ብር 50,000 (አምሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የዋርካ ሜዲካል እና ቢዝነስ አክሲዎን ማህበር ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
10. አሸናፊው ተጫራች በጥራት G+0 እና G+4 እና B+G+4 ሌሎች ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ እና ለተለያዩ ቢዝነስ አገልግሎት ማለትም ለመሰብሰቢያ አዳራሽ ለባንክ ለኢንሹራንስ እና ለሌሎች ቢዝነስ አገልግሎቶች የሚዉሉ ህንፃዎች የተለያዩ ክፍሎች ዲዛይን በጥራት ሰርቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከዚህ በፊት የሆስፒታል ዲዛይን ሰርቶ የሚያዉቅ ተጫራች እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
11. የሚሰራዉ ዲዛይን የጤና ሚኒስቴር ለጀኔራል ለጠቅላላ ሆስፒታል እና ቲችንግ ሆስፒታል ያወጣዉን ሁሉንም መስፈርት ያካተተ እና ያሟላ መሆን አለበት፡፡
12. በተጨማሪ በሆስፒታሉ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
13. የአፈር ናሙና ጥናት በራሱ ወጭ ሊያስጠና የሚችሉ፡፡
14. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የዋርካ ሜዲካል እና ቢዝነስ አክሲዎን ማህበር ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 28 79 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዋርካ ሜዲካል እና ቢዝነስ አክሲዎን ማህበር