Addis Zemen (Apr 08, 2026)
የጨረታ ቁጥር 03/2018
በአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የፋ አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት በፑላችን ስር ለሚገኙ ለተለያዩ ጽ/ቤቶቹ አገልገሎት የሚሰጡ አላቂ እቃዎች የኤሌክትሪክ መኪና ኪራይ፣ ኤሌክተሮኒክስ (ቲቪ) በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረዉ መሠረት መስፈርቱን ከምታሟሉ ተወዳዳሪዎች አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
5. የጨረታ ሠነዱን አራት ኪሎ በሚገኘው የክ/ከተማው አስተዳደር ህንፃ በዋና ሥራ አስፈጻሚ የፋ/አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ 9ኛ ፎቅ 902 ቁጥር ጋዜጣዉ ከወጣበት ቀን 2018 ዓ.ም እስከ አስረኛው /10/ የሥራ ቀን 2018 ዓ.ም ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ዘዉትር በሥራ ቀን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መዉሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ በማዘጋጀት እና በማሸግ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ እስከ 11ኛዉ የሥራ ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ባለዉ ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሸጎ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዋና ሥራ አስፈፃሚ የግዥ ቡድን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል።
8. ተጫራቾች የጫረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በየዘርፉ በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣በፍሉድ የጠፋ ነድ ከጨረታዉ ይሰረዛል።
10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የአጠቃላዩን ብር 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
12. በጥቃቅን ተደራጅተዉ በዘርፉ ለተሰማሩ ተጫራቾች የተገለጹትን ቁሳቁሶች እቃዎች የአምራችነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ይህ ካልሆነ እንደማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሠነድ መግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የአስ/ፋ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን