በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አላቂ የህክምና አቅርቦቶች ግዥ እና የህክምና ዕቃዎች ጥገና ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አላቂ የህክምና አቅርቦቶች ግዥ እና የህክምና ዕቃዎች ጥገና ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 08, 2026)

የጨረታ ስታወቂያ

የእቃ ግዥ ጨረታ፣ ጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/ቁ/05/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች 2018 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

  • ሎት 1አላቂ የህክምና አቅርቦቶች ግዥ፣
  • ሎት 2 የህክምና ዕቃዎች ጥገና፣ ለአንድ አመት ውል የሚፈረም ግዥ፣

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልግ ተጫራች፡

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፍቃዱን ያደሰ፤

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና፣ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

3. የአቅራቢነት ማስረጃ ያለው፤

4. ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሣተፍ የጨረታ ማስከበሪያ

  • ሎት 1አላቂ የህክምና አቅርቦቶች ግዥ 100,000.00 ብር
  • ሎት 2የህክምና ዕቃዎች ጥገና፣ ለአንድ አመት ውል የሚፈረም ግዥ 10,000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

6.አሸናፊ ተጫራቾች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ክምችት (የራሱ ስቶክ) ያለውና፤ እቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ (ወጪ) እስከ ሆስፒታሉ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ አምጥቶ እና በራሱ ወጪ አውርዶ : ማስረከብ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ መረጃቸውን እና፣ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት መምጣት ይኖርባቸዋል፤ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋት 230 እስከ 1000 ሰዓት በሆስፒታሉ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር አዲስ (በመኪና መግቢያ በር ገብቶ ወደ ግራ እጥፍ ብለው በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ የሎት ቁጥሩ፤ ሰነድ ሲገዙ የተሰጣቸው መለያ ኮድ ፅፈው፣ የድርጅታቸው ህጋዊ ማህተም መተው፤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ጨረታቸው አንድ (1) ኤንቨሎፕ ነው።ኦርጅናል እና ኮፒ ለይተው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው 10 ቀናት የአየር ላይ ቆይታውን እንዳጠናቀቀ በ11ኛው ቀን ጠዋት 300 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።

9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው ሆስፒታላችን በሰጠው መሙያ ቅጽ ብቻ መሙላት ይኖርባችኋል፤ ማንኛውም ስርዝ ድልዝ፤ ማህተም ያልተደረገበት የቀረበ ዋጋ፤ በሆስፒታሉ ዋጋ መሙያ ቅጽ ያልተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም። ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።

10.ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡በአራዳ ጊዮርጊስ / ወደ አስኮ የሚወስደው መንገድ ከዮሐንስ / 500 ሜትር አለፍ ብሎ እንገኛለን።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፤

አድራሻ፡ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ከዮሐንስ / 500 ሜትር አለፍ ብሎ እንገኛለን። ለተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥር 0111112056 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *