Reporter (Apr 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ. |
የተበዳሪው ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የንብረት አስያዥ ስም |
የቦታ አገልግሎት |
ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የካርታ ቁጥር |
የቦታ ስፋት በካ.ሜ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የጨረታ ቀን |
የጨረታ ሰዓት |
||
|
ከተማ |
ክፍለ ከተማ |
ቀበሌ/ ወረዳ |
||||||||||
|
1 |
ማርቁማ አግሮ ኢንደስትሪ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር |
ኮከብ |
ትእግስት አቦማ |
ለመኖርያ ቤት |
አ.አ |
ለሚ ኩራ |
10 |
ቦሌ10_1/56/3/13+ 1/36730/250512/03 |
200 |
28,166,220 |
4/9/18 |
4:00-5:00 |
|
2 |
ዮሀንስ ገዛኀኝ |
ቦሌ አራብሳ |
ተበዳሪው |
ለመኖርያ ቤት (ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም 295/23) |
አ.አ |
ለሚ ኩራ |
10 |
AA000061007 3132950223 |
37.16 |
2,403,025 |
4/9/18 |
5:00-6:00 |
|
3 |
ሁንዴ ዱጋሳ |
ፊንፊኔ |
ተበዳሪው |
ለመኖርያ ቤት( ሲሲዲ ጊቢ ውስጥ የሚገኝ) |
ሸገር |
ለገጣፎ |
|
L/X/L/D/3650/00 |
1098.62 |
28,715,367 |
4/9/18 |
8:00-9:00 |
|
4 |
አማኑኤል ጡዴ |
ቢርቢር |
ተበዳሪው |
ለመኖርያ ቤት |
ቢርቢር |
|
|
INR-83 |
250 |
234,400 |
4/9/18 |
5:00-6:00 |
1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል::
2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 -3 የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ባለዕዳው ወይም ሕጋዊ ወኪሉ፣ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት የባንኩ ዋናው መ/ቤት ጊዜያዊ ጽ/ቤት በሚገኝበት ህንጻ ውስጥ ይካሄዳል:: በተራ ቁጥር 4 የተዘረዘሩት ንብረቶች ጨረታ ደግሞ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ንብረቶቹ በሚገኙበት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል:: ተበዳሪው/አስያዡ በጨረታው ቀን ባይገኙም ሃራጁ በተያዘለት ቀን/ጊዜ ይካሄዳል፡፡
3. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ግን ባንኩ ዋጋውን የሚቀበል መሆን አለመሆኑን ጨረታው ከተደረገበት ቀን ቀጥሎ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለተጫራቹ ያሳውቃል::
4. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የአሸናፊነት ደብዳቤ ከባንኩ ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል::
5. ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል::
6. ከተገነባ ሁለት አመት ከሞላው መኖሪያ ቤቶች ውጭ ባሉ ንብረቶች ሽያጭ ላይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የሚታሰብ ሲሆን ሁሉንም ንብረቶች በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያ ገዢ ይከፍላል::
7. ለተጨማሪ መረጃ::- ኮከብ ቅርንጫፍ 011-667-44-63፣ ቦሌ አራብሳ ቅርንጫፍ 011-813-20-63፣ፊንፊኔ ቅርንጫፍ 011-557-02-00፣ ቢርቢር ቅርንጫፍ 046-452-06-78 ወይም የሕግ አገልግሎት 0115-57-00-75/0115570135 ብሎ መደወል ወይም በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል::
8. ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አዋሽ ባንክ