በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ለሚጠቀምባቸው የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ለሚጠቀምባቸው የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 09, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ///// 02/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን 2018 በጀት ዓመት ለሚጠቀምባቸው የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

1. ሎት 1የላፕቶፕ ግዥ

2.ሎት 2የኤሌከትሪክ መኪና ኪራይ ግዥ

3. ሎት 3 የመኪና ጎማ ግዥ

4. ሎት 4 የደንብ ልብስ

5. ሎት 5 የግብርና ግብዓት ግዥ

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና የፋይናንስ መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ሎት/ምድብ በኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (የተመዘገበበት ቀን፣ አቅራቢነቱ ከመስኩ ጋር የሚመሳሰል፣ የባለቤትነት የሚገልጽ) የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ተጫራቾች በገቢዎች ሚኒስቴር በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ መረጃ /ክሊራንስ/ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10/አስር/ የሥራ ቀናት እስከ 1100 ሰዓት ድረስ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 በመቅረብ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታውም 10ኛው ቀን 1100 ሰዓት ታሽጎ 11ኛው ቀን 400 ሰዓት ላይ በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ /7ተኛ ፎቅ/ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 400 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡

7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔፊኬሽኑ መሰረት ብቻ ሞልተው በየሰነዳችሁ ኮፒ ላይ በመፈረም የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ፤ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው 4 ፖስታ በማሸግ ፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በደንብ አሽገው ኤንቨሎፕ ላይ ኮፒና ዋና ሰነድ ብለው በመለየት የግዥ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8. በአንድ ምድብ የምትጫረቱ ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ምድብ ፖስታው ላይ በመግለፅ የተጫረቱበት ምድብ /ሎት 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሌሎች ሕጋዊ ሰነዶች ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ከአንድ በላይ በሆነ ሎት /ምድብ የምትጫረቱ ተጫራቾች የምትጫረቱበት ሎት/ምድብ በመግለጽ ለየብቻ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ፖስታ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባችኋል። ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ሎት ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ 2% ሲፒኦ በማሠራት ለሎቱ በተዘጋጀው ኦሪጅናል ሰነድ የያዘ ፖስታ ውስጥ በማስገባት የሎት ቁጥርና መጠሪያ በፖስታ ጀርባ ላይ በመፃፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

10. በሎት/ምድብ 1 ላይ ለወጡ ላፕቶፖች ኮሚሽኑ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት በባለሙያ ተረጋግጦ የሚረከብ ይሆናል ፡፡

11. በሎት/ምድብ 2 ላይ ለወጡ የመኪና ኪራይ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን መኪኖች ኮሚሽኑ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት የሚያቀርቡ ሲሆን መኪኖቹ ለኮሚሽኑ ከቀረቡ በኋላ በኮሚሽኑ ስምሪት እና ኮሚቴዎች በቀረበው ስፔስፊኬሽን አረጋግጦ የሚያሳልፍ ይሆናል፡፡

12. በሎት/ምድብ 3 ላይ ለወጡ ጎማዎች ኮሚሽኑ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት በባለሙያ ተረጋግጦ የሚረከብ ይሆናል ፡፡

13.በሎት/ምድብ 4 ላይ ለወጡ ደንብ ልብስ ኮሚሽኑ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት በጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ የሚረከብ ይሆናል ፡፡

14. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች ካደራጃቸው ተቋም የጨረታ ሰነድ በነፃ እንዲወስዱና ለጨረታ ማስከበሪያ እንደሚያገለግል የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

15. ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡

16. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

17. ተጫራቾች ተቋሙ ካቀረበው ስፔስፊኬሽን ውጭ ሌላ ስፔስፊኬሽን መጨመር፣ መቀነስ ወይም ሰርዞ ማስተካከያ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡

18. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ ///// 22 መክሊት ሕንፃ ፊት ለፊት ያሬድ ቶርኖ ቤት ሕንፃ ላይ 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 404

ስልክ ቁጥር፡ 011 165 90983

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን