በኢፌዴሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እ.ኤ.አ በ2026 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውል የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች (ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ዓርማ የሚታተምባቸው ቲሸርቶች፣ እስክሪብቶ፣ አጀንዳ፣ ቢልቦርድና እና ሌሎችም) ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢፌዴሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እ.ኤ.አ በ2026 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውል የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች (ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ዓርማ የሚታተምባቸው ቲሸርቶች፣ እስክሪብቶ፣ አጀንዳ፣ ቢልቦርድና እና ሌሎችም) ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 09, 2026)

የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች (ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፐሪንተር፣ ዓርማ የሚታተምባቸው ቲሸርቶች፣ እስክሪብቶ፣ አጀንዳ ፣ቢልቦርድና እና ሌሎችም) ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ ስተአ/003/2026

የአገልግሎት /ቤታችን .. 2026 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውል የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች (ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ዓርማ የሚታተምባቸው ቲሸርቶች፣ እስክሪብቶ፣ አጀንዳ ፣ቢልቦርድና እና ሌሎችም) ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚፈለግባቸውን ማንኛውንም የመንግሥት ግብር አጠናቅቀው ለመክፈላቸው ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ፣የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ በጨረታ ለመሳተፍ በኢ... መንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በአቅራቢነት የተመዘገቡ እንዲሁም የተ... ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን፣ በብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ውል በመግባት የሚፈፀም ይሆናል።

በመሆኑም ተጫራቾች፡

1) የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ አራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 4 እንቁላል ፋብሪካ ወይም የፌዴራል ፖሊስ ክብብ ፊት ለፊት ከሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና /ቤት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመምጣትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ለ10 ተከታታይ ስራ ቀናት ከጠዋቱ 230 ሰዓት እስከ 630 ሰዓት ከሰዓት 730 እስከ 1130 ባለው ጊዜ ውስጥ መግዛት ይቻላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ስራ ቀናት አይደሉም።

2) ማንኛውም ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጥቅል ዋጋ 2/ሁለት/ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና .D.RE Refugees and Returnees Service ስም በተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ፣ የአገልግሎቱን ዋጋ፣ በቀረበው ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ መሰረት የቴክኒክ ሰነድ እና እንዲሁም በጨረታ ሠነዱ የተዘረዘሩትን የብቃትና የልምድ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚያያዙ ማስረጃዎች በሙሉ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላበቃላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

3) የመጫረቻ ሠነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አስከ 10ኛው የስራ ቀን 800 ሰዓት ድረስ ከታች በተመለከተው አድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የሰራተኞች ክበብ ምድር ቤት ይከፈታል። ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ፣ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

4) መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ

ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 0997-23-6631

በኢፌዴሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *