የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማ ልማትና ኮንስ/ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት ለአረንጓዴ ልማት እንክብካቤ የሚሆን የሳር ማጨጃ ማሽን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማ ልማትና ኮንስ/ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት ለአረንጓዴ ልማት እንክብካቤ የሚሆን የሳር ማጨጃ ማሽን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 09, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ////መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማ ልማትና ኮንስ/ መምሪያ 2018 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት ለአረንጓዴ ልማት እንክብካቤ የሚሆን የሳር መጨጃ ማሽን ግዥ ለመፈጸም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አወዳድሮ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት፡

1.በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች

2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

4. በጨረታው እንዲሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት

5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተ ዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ /በባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረ/ .. c.p.o ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡

7. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ እና ከላይ የተጠቀሱትን ቴክኒካል ቅድመ ግምገማ ሰነዶችን አሟልቶ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. አስፈላጊ የሆኑ ቴክኒካል ጉዳዮች በሚሸጥ ሰነድ ውስጥ በተቀመጠው መስፈርት መሠረት የሚገመገም ስለሆነ በጥንቃቄ መዘጋጀት ይጠበቅበታል፤

9. ጨረታው 11ኛው ቀን ከቀኑ 330 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4.00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ፡፡

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡ 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ//መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *