በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 11, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ቦሌ/ክ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት 002/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ /ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

  • ሎት አንድ፡የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት ሁለት: የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት ሦስት: የተለያዩ የመኪና ማስዋቢያ ዕቃዎች
  • ሎት አራት:- ልዩ ልዩ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
  • ሎት አምስት፡የተለያዩ የደንብ ልብሶች
  • ሎት ስድስት፡ቋሚ ዕቃዎች

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል

1. ከሚወዳደሩበት ዕቃ ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር ለመወዳደር ተያያዥነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃዎችን(ክሊራንስ) ከግብር አስገቢው /ቤት ማቅረብ የሚችሉ::

2. በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት ግዥ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::

3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::

4. የሀገር ውስጥ የድጋፍ አቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት (በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት) የተደራጁ መሆኑን እና ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለአጠቃላይ ከሎት አንድ እስከ ሎት ስድስት 2% ለእያንዳንዳቸው ሎቶች በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ CPO መሥራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለቦሌ //አነስተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት፡፡

6. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መክፈቻው ቀን ድረስ አንበሳ ጋራዥ በስተጀርባ ከሚገኘው የቦሌ /ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት ከግዥ ቡድን አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያጠቃለለ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባችሁ፡፡

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በመ/ቤቱ አዳራሽ 4ተኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል። እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታ መወዳደር በሚቀርብበት ወቅት ኦርጅናል እና ኮፒ የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር/በተለያየ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ኮፒ እና ኦርጅናል ተለይቶ በፖስታዉ ዉጫዊ ገጽ መጻፍ አለበት።

8. ሰነዱን በሚመልስበት ወቅት ሥልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ መያያዝ አለበት።

9. አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም

10. የጨረታው አሸናፊ የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሰው የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር ፐርሰንት) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።

11. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎችንም ለንብረት አስተዳደር ክፍል ማስረከብ አለባቸው።

12, የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ጀምሮ 90 ቀናት መቆየት አለበት።

13. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011-639 -42-45/

አዲስ አበባ አስተዳደር ከተማ አስተዳደር ቦሌ /ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት