Addis Zemen (Apr 12, 2026)
የጨረታማስታወቂያ ቁጥር 001/2018
የፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አዲስ በማስገንባት ላይ ላለው የህንፃ ቤተክርሲቲያን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ልዩ ልዩ ሥራዎች በግራናይት በላይምስቶን እና በባዛልት ዘመኑን በዋጀ የማሽን አቀራረጽ በማስቀረፅ ለማሠራት ይፈልጋል።
- በለሰለሰ ሁኔታ የተቀረጸ የውጭ ግድግዳ ግራናይት ልባስ (ክላዲንግ)
- የቨራንዳ አምዶች (column) የላይም ስቶን ልባስ (ከላዲንግ)
- የመስኮት እና የበር ፍሬም (በላይምስቶን)
- የባዛልት ድንጋይ በቤዝ ፍሬም (ዘኮሎ)
- የወገብ አካፋይ ፍሬም(መቀነት) በግራናይት
1. የሥራው ዘርፍ
ተጫራቾች በሚከተሉት አማራጮች ተለይተው በቀረቡ ምድቦች ላይ መወዳደር ይችላሉ፦
- ምድብ ፦የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እና ገጠማ
- ምድብ 2፦የገጠማ /የእጅ/ሥራ ብቻ
- ምድብ 3፦የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ብቻ
ተጫራቾች አንድም ሆነ ከዚያ በላይ በሆኑ ምድቦች ላይ መሳተፍ ይችላሉ
2. ተጫራቾች ሲያሟሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ መስፈርቶች
- በዘርፉ የታደሰ የንግድና የሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ።
- በተመሳሳይ የቤተክርስትያን ሥራዎች ላይ በቂ የሥራ ልምድ ያላቸው እና የመልካምሥራ አፈጻጸም ማስረጃቸውን በፎቶግራፍ አስደግፈው ማቅረብ የሚችሉ።
- ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የድንጋይ ቅርፅ ማውጫ ማሽነሪና የወርክሾፕ አደረጃጀት ያላቸው።
3. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድና አቀራረብ
ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን
ከቤተክርስቲያኑ የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ ጽ/ቤት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት መውሰድ ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን በሁለት ቅጂዎች (አንድ ዋናና ሁለት ቅጂዎች) ለየብቻ በሰም በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የጠቅላላዋጋውን 2% በሲፒኦ (CPO) ወይም በባንክዋስትና በፈረንሳይ ደብረፀሐይ ቅዱስጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
4. የጨረታመዝጊያናመክፈቻ
ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ፣ በዚያው ቀን ከቀኑ 4፡ዐዐ ተዘግቶ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቤተክርስቲያኑ ሰበካ ጽ/ቤት ይከፈታል።
5. ልዩ ማሳሰቢያ
- ማንኛውም ተጫራች የግንባታ ሂደት ጉብኝት (Site Visit) የማድረግ ግዴታ ያለበት ሲሆን ፣ የቴከኒክ ምዘናው ውጤታቸው ከ70% በላይ ለሆኑ ተጫራቾች ብቻ የፋይናንስ ሰነዳቸው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ተወዳዳሪዎች የስራ ቦታ (work shop) እና የሰሩዋቸው ስራዎች በቴክኒካል ግምገማ ወቅት በጨረታ ኮሚቴ ይጎበኛሉ።
- የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ግምገማ ድምር ውጤት ከፍተኛ ነጥብ ያመጣ ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ይሆናል።
- ተጫራቾች ለናሙና የሚሆን የግራናይት ቅርፅ በደብሩ ግቢ ውስጥ ሠርተው ማሳየት ይኖርባቸዋል።
- ቤተክርስቲያኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02
ስልክ ቁጥር 0911223523/ 0911231951
በፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ