አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የተለያየ መጠን ያላቸውን የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የተለያየ መጠን ያላቸውን የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Reporter (Apr 12, 2026)

የፅህፈት መሣሪያዎች የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች

እንዲሁም የህትመት ውጤቶች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር AIC-0014/2026

ኩባንያችን የተለያየ መጠን ያላቸውን የፅህፈት መሣሪያዎች የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

. ሎት -1 የፅህፈት መሣሪያዎች

. ሎት-2 የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች

. ሎት-3 የህትመት ውጤቶች

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እንዲሁም ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም::

3. ከላይ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለጸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሲፒኦ (CPO) ሙሉ ለሙሉ ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊው ድረጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ለኩባንያው ገቢ ካደረገ በኋላ ኩባንያው የገቡትን እቃዎች በሳምፕላቸው መሰረት መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ነው::

4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኩባንያው ዋና /ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ::

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል::

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ሚያዚያ 5 ቀን 2018 . እስከ ሚያዚያ 9 ቀን 2018 . ከቀኑ 900 ድረስ ቦሌ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ . ዋና /ቤት ህንፃ 11 ፎቅ በስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::

7. ጨረታው ሚያዚያ 9 ቀን 2018 . ከቀኑ 930 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና /ቤት ህንፃ 11 ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ/ስልጠና አዳራሽ ይከፈታል::

8. ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ የእቃው ዝርዝር መግለጫ (Specification) የያዘ ሊሆን ይገባል እንዲሁም በሚያቀርቡት ናሙና (Sample) ላይ የድርጅታቸው ማህተም ሊኖር ይገባል::

9. አንዱ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚያሳግድ መሆኑን እንገልፃለን::

10. አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች 7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንዲሁም የህትመት ውጤቶች 15 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ወይም በውሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል::

11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ሲወዳደሩ ባስገቡት (ባቀረቡት) ሳምፕል / ናሙና እንዲሁም የህትመት ውጤት በኩባንያው ናሙና መሰረት መሆን አለበት::

12. ተጫራቶች ያሸነፉትን እቃ እንዲሁም የህትመት ውጤቶች የኩባንያው ዋና /ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል::

13. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ :- በስልክ ቁጥር 0116 611 877 / 0116 637 485 / 0116 637 716 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::

አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ (ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊት ለፊት) አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *