የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ወርክ ስቴሸን/ Work-station/ ኮምፒውተር በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ወርክ ስቴሸን/ Work-station/ ኮምፒውተር በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 14, 2026)

ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 1744/ሲ/ብ/ክ/መ/ኮ/ቢሮ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ወርክ ስቴሸን/ Work-station/ ኮምፒውተር በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ፡-

  • ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፊቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማቅረብ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ እንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ተያይዟል።
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  • የጨረታ ሰነዱ በተጨራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተው በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት 10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 4፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት 10ኛው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 4፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  • የጨረታው መዝግያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል::
  • ተጫራቾች መመሪያ ባለማክበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ሀላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያካትት መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል።
  • አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው። በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመመጣጠን ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል። በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካል ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።

ቢሮው የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ብሮ ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *