የምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት 00 ጠጠር እና 01 ጠጠር፣ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት 00 ጠጠር እና 01 ጠጠር፣ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Apr 13, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት ማለትም፡- ሎት 1. 00 ጠጠር እና 01 ጠጠር፣ ሎት 2 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና በጨረታዉ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ደብረ ማርቆስ በሚገኘው ምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት አብማ መስመር ዶ/ር ይልቃል ዓይን ህክምና ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከቢሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበት የስራውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ  ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ የጨረታ ሰነዱን ሞልተዉ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

7. ጨረታው በ7ኛው ቀን 9፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡ በዚያዉ ቀን 10፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ምሥራቅ ጐጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 34 05 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አልማ ልማት ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *