Be'kur (Apr 13, 2026)
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ ተስፋለም ባዩ ደሴ ፣ጠበቃ ገረመው ምስጋናው እና በአፈ/ተከሳሽ መኮነን መስፍን አበበ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ ፤ንብረትነቱ የአፈጻጸም ተከሳሽ የሆነውን ፤በቡሬ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 02 የሚገኘውን በምስራቅ ታፈረ ክንዴ፣ በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን ውብርስት ተረፈ እና በደቡብ የወሬው ነጋ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው 250 ካ/ሜትር ቦታ ላይ የተሰራ ቤት ፤ግምቱ 2‚890‚000 (ሁለት ሚሊዩን ስምንት መቶ ዘጠና ሽህ) ብር ሆኖ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ ተጫራቾች የግምቱን ¼ኛ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9900011059086 በሆነ በሞዴል 85 በሲፒኦ በማስያዝ ቡሬ ከተማ ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል።
የቡሬ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት