የቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ


Be'kur (Apr 13, 2026)

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሣሽ ሣምራዊት ግሮሰሪ እቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሣሾች

1ኛ. አለኸኝ ሙሉነህ፣

2ኛ. ቦጋለ ክንዴ፣

3ኛ. ሀብታሙ መኩሪያው መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ  አዋሣኝ በምስራቅ ተሰራ ካሣ፣ በምዕራብ ቃል ኪዳን አየን፣ በሰሜን የሻረግ አሞኝ እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል ያለ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 622,133.14 (ስድስት መቶ ሃያ ሁለት ሽህ አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ከአስራ አራት ሣንቲም) ይሸጣል፡፡

ጨረታውን ከሚያዚያ 18/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም በጋዜጣ በማዋል ጨረታው ግንቦት 22/2018 ዓ.ም ከከረፋዱ 3፡00 እስከ 5፡00 የሚከናወን ሲሆን በወቅቱ ጨረታ አሸናፊ ከተገኘም 1/4ኛውን ወዳያውኑ በከፍ/ፍ/ቤቱ የአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9900017292928 በሆነ ገቢ እንዲያደርግ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ አንዲቀርብ በማድረግ በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በቦታው ተገኝተው መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

የአዊ ብሔ/ዞን/ከፍ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *