የአብክመ ውሀና ኢነርጅ ቢሮ እና ማእድን ሀብት ልማት ቢሮ በመደበኛ በጀት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፎቶ ካሜራ፣ የጽዳት እቃዎች እና የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአብክመ ውሀና ኢነርጅ ቢሮ እና ማእድን ሀብት ልማት ቢሮ በመደበኛ በጀት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፎቶ ካሜራ፣ የጽዳት እቃዎች እና የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Apr 13, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-007/2018 

የአብክመ ውሀና ኢነርጅ ቢሮ እና ማእድን ሀብት ልማት ቢሮ በመደበኛ በጀት ሎት 1.የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት2.ፎቶ ካሜራ፣ ሎት3. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት4.የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፤

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆን አለባቸው።

2. የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሎት1. 50,000 (አምሳ ሽህ) ብር ፣ለሎት2  እና ሎት 4. 30,000 (ሰላሳ ሽህ )ብር፣ ለሎት 3. 5,000 (አምስት ሽህ ) ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።

6. በጨረታው ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100 (አንድ  መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ለየብቻ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን  8፡00  ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ  ይከፈታል።

8. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10.  ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 0132/058 220 1087 ዘወትር በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ።

11.  አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቀበሌ 07 ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት  ይገኛል።

የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *