Be'kur (Apr 13, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጓንጓ ሽኩዳድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለጓ/ሽ/ወ/ አስተዳደር ቢሮ ግንባታ
- ሎት 1. የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ የሙያ (ጉልበት) ፣
- ሎት 2. አስተዳደር ቢሮ የግንባታ ማቴሪያል፣
- ሎት 3. አችጊ ጤና ጣቢያ የግንባታ ማቴሪያል በሎት ጥቅል ማሰራት (መግዛት) ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ፈቃድና የቲን ተመዝጋቢ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡2. ስለ ቢሮ ግንባታው እና ግንባታ ማቴሪያል እቃው የተዘጋጀውን (ስፔስፊኬሽን) በትክክል በማጥናት በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል መሞላት አለባቸው ሥርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት የለውም፡፡
3. ደረጃ 05 /አምስት/ እና በላይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. በዚህ 3 ዓመት ውስጥ በተመሳሳይ ሙያ የሰራ መሆኑን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. በዋጋው ማቅረቢያ ላይ የተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪል ስም፣ ፊርማና የድርጅቱ አርማ ያለው ማህተም መኖር አለበት፡፡ በተጨማሪ በፖስታው ላይ ያጫራቹን መ/ቤት ስምና የራሳቸው አድራሻ በትክክል ማስቀመጥ አለበት፡፡
6. በሌላው ዋጋ ተንተርሶ መወዳደር አይፈቀድም፡፡
7. የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ፖስታዎች ላይ የንግድ አድራሻውንና ስሙን በመግለጽ በደንብ በታሸገ ፖስታ የሞላዉን ዋጋ ኦርጅናል ፖስታ የጓ/ሽ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ን/አስ/ ቡድን ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
9. የጨረታ ማስከበሪያ ከቀረበዉ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ (ቢድ ቦንድ) ወይም በመሂ 1 በማስያዝ በፖስታዉ ዉስጥ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ከጨረታዉ ይሰረዛሉ፡፡
10. በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ገንዘብ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ውል ከወሰደ በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡
11. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ በሚቀጥሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉ 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የዉል ማስከበሪያ ካሸነፈዉ ከጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (ቢድ ቦንድ) ወይም በመሂ 1 በማስያዝ ዉል መያዝ ይኖርበታል፡፡
12. በጨረታ ውድድር ወቅት ቅር የተሰኘ ተጫራች አሸናፊው በተገለፀለት 5 የስራ ቀናት ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
13. ማንኛውም ተጫራች ያለ በቂ ምክንያት ውሉን ካፈረሰ ያስያዘውን ገንዘብ በመቀጫ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ በህግም እንዲጠየቅ ያደርጋል፡፡
14. የጨረታው ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ውድድር ጥያቄ ወይም የማስተካከያ ተቀባይነት የለውም ጨረታው ከመታሸጉ በፊት ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል ይችላሉ፡፡ ያሳይሆን ቢቀር ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም፣
15. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳችውን ማግለል አይችሉም፡፡
16. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊቱ በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ እንደሚያደርግና ያስያዙት ገንዘብ እንደሚወረስ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
17. ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ይቆይና፤ በ22ኛው (ሃያ ሁለተኛው) ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የሚፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
18. መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
19. የጨረታ ሠነዱን ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
20. የማቴሪያል ማስረከቢያ ቦታ ጓ/ሽ/ወ/ ንብረት ክፍል እና አችጊ ጤና ጣቢያ ግንባታ ማስረከብ የሚችሉ፡፡
21. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
22. ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልገዎ በስልክ ቁጥር 058 229 00 50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጓንጓ ሽኩዳድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት