ፀደይ ባንክ አ.ማ. ለምቾት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውን መኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ፀደይ ባንክ አ.ማ. ለምቾት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውን መኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Apr 15, 2026)

2 ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ . ለምቾት /የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና ዝርዝር ሁኔታቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የተበዳሪ ስም

የንብረት አስያዥ ስም

የንብረ መገኛ እና ካርታ ቁጥር

መነ ግምት

1

ምቾት /የተ/የግ/ማህበር

አቶ ታፈረ ወርቁ መራ

በአብክመ በቡሬ ከተማ ቀበ 03 የሚገኝ ካርታ ቁጥር 16421/2013 መኖሪያ ቤት

2,487,661.37

2

ምቾት /የተ/የግ/ማህበር

አቶ ታፈረ ወርቁ መራ

በአብክመ በቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኝ ካርታ ቁጥር 16422/2013 መኖሪያ ቤት

1,831,779.94

3

ምቾት /የተ/የግ/ማህበር

አቶ ታፈረ ወርቁ መራ

በአብክመ በቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኝ ካርታ ቁጥር 9005//2008 መኖሪያ ቤት

2,119,342.42

በመሆኑም ማንኛቸውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ደንቦችና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች በጫራታው እንዲሳተፉ እንጋብዛለን።

1. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ) በፀደይ ባንክ . ስም በማሰራት ለጨረታ መስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል

2. በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱን መመስረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል

3. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል

4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: አሸናፊው 15 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ያሆናል።

5. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ይመለስላቸዋል

6. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ፣ግብር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ይሸፍናል:: ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዡ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።

7. ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ

8. ጨረታው ግንቦት 11 ቀን 2018 . ከጥዋቱ 300 እስከ 600 ፍኖተሰላም ከተማ ከሚገኘው የፀደይ ባንክ ፍኖተ ሰላም ዲስትሪክት ቢሮ ግራውንድ ይደረጋል

9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918 560 275


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *