Addis Zemen (Apr 18, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ የሰራተኛ ሰርቪስ የሚሆን ኮስትር መኪና የኪራይ አገልግሎት ከአቅራቢ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን።
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፍኬት/የሚያቀርብ።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰረተፍኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት።
- ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- የተሽከርካሪው የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኮፒ ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 30,000.00/ ሰላሳ ሽህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና የሚያስይዝ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት/15/ ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 113 ድረስ በአከል ቀርቦ መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሸገ ፖስታ በማድረግ አ.ብ.ክመ ጤና ቢሮ ግዥ ፋይ/ ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ግዥ ከፍል ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥ ከፍል ጃይካ ሀንፃ ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን በ 8:30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ቢሮው የግዥዉን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈውን የመኪና ኪራይ አገልግሎት በተባለው ቀን ይዞ መቅረብ አለበት።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ቁጥር ጃይካ ህንፃ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 1127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ