Reporter (Apr 22, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/31/18
የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለስልጠና ማዕከል የምግብ እና የሻይ፣ ቡና እንዲሁም ውሃ አቅርቦት ግዥ ተጫራቾችን አወዳድሮ ስራ ማሰራት ተፈልጓል።
በዚህም አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ድርጅቶችን በሀገር ዓቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት የመሳሰሉትን የቴክኒክ ሰነዶች በተለየ የታሸገ ፖስታ እንዲሁም ፋይናንሻል ዶኩመንት በተለየ ሁለተኛ የታሸገ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ማግኘት ይቻላል:: የጨረታ ማስከበሪያ ለስልጠና ማዕከል የምግብ እና የሻይ፣ ቡና እንዲሁም ውሃ አቅርቦት ግዥ ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ሀንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569982
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ