የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ የጥበቃ እና ፍተሻ አገልግሎት የሚሰጡ ኤጀንሲዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዢ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ የጥበቃ እና ፍተሻ አገልግሎት የሚሰጡ ኤጀንሲዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዢ መፈፀም ይፈልጋል


Reporter (Apr 22, 2026)

   የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCDE 009/2018

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ የጥበቃ እና ፋተሻ አገልግሎት የሚሰጡ ኤጀንሲዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡

  1. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የገበሩበትን ንግድ ፈቃድ .. (VAT) ወይም የሽያጭ ታክስ (Turn over Tax) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው በደንቡ መሠረት ከመንግስት የግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣ በማንኛውም ጨረታ ለመሳተፍ የሚችል Tax Clearance እና ሌሎች ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው:: በተጨማሪም በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ የታገዱ ድርጅቶች ዲዛይን ድርጅቱ መረጃውን ካገኘ በጨረታ እንዳይሳተፉ ወይም ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ ይደረጋል።
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዐት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 230- 630 ከሰዐት 730-1100 እስከ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ 4 ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  5. ጨረታው ከሚያዝያ 14 ቀን 2018 እስከ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 .. አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ሚያዝያ 23 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም።
  6.  የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል።
  7. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል።

አድራሻ፡የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23

አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን

የነበረበት የኪያሜድ ኮሌጅ ህንጻ አራተኛ ፎቅ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *