Addis Zemen (Apr 22, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018
የማ/ኢ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የ2019 ዓ.ም ቀን መቁጠሪያ የጠረጴዛ ካላንደር፣የችሎት አጀንዳ እና መደበኛ አጀንዳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡–
1. የዘመኑን ግብር ከፍለው ንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ እና የታደሰውን ንግድ ፈቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ በማድርግ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ተወዳደሪዎች ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
3. ተጫራቾች 9,000.00 (ዘጠኝ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ቢድ ቦንድ ማስያዝ የሚችሉ ሲሆን ቢድ ቦንድ የሚያሲዙት ከሆነ ከ90 ቀን ያላነሰ ጊዜ ያለው ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. የተዘጋጀው ጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምር ለተከታተይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 22 መግዛት ትችላላችሁ፡፡
5. ከተቋማችን የገዛችሁትን ቴክኒካል ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ የድርጅታችሁን ማህተም በማሳረፍ በድርጅቱ ስራአስኪያጅ ተፈርሞ ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ በሰም በታሸጉ ፖስታዎች አድርጋችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
6. ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. የጨረታ ዋጋ እና የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ የሚቆጠር ከ45 ቀን ያላነሰ መሆን አለበት፣
8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶቹ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
9. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለግዎ በስልክ ቁጥር 046-556 1645 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የማዕ/ኢ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት
ሀላባ ቁሊቶ