Addis Zemen (Apr 23, 2026)
የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ መኢአግ/ግጨተሸ/02/2018
1. የግዥ ፈፃሚው ስም መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንደሰትሪ ግሩፕ/መኢኢግ/
2. የግዥው ዓይነት: ሎት አንድ ፡– የኤሌክትሪካል ተሽከርካሪ ግዢ
3. በጨረታው መሳተፍ · የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡– የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TN Number) እና በኢፌዴሪ የመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢነት ኦን ላይን የተመዘገበና የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
4. የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ፡ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንደሰትሪ ግሩፕ በአቅርቦት ሰንሰለት አሰተዳደር ዳይሬክቶሬት በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 102 እና 105 ሀይሌ ጋርመንት የቀድም ሪቬራ ሆቴል ማግኘት ይችላሉ።
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን፡–ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በእያንዳንዱ ሎት የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ወይም በሁኔታዋች ላይ ያልተወሰነ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Performance bond) ተጫራቹ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% (10 ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ሲያቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያው የአሸናፊ መግለጫ ይለቀቅለታል።
7. የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የሚከፈል የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በገንዘብ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይቻላል።
8. የመወዳደሪያው ሰነድ የሚቀርበው ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል፣ ፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል የድርጅታችሁ ማህተም የተመታበት፣ ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ የቅጂ ብዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ አንዳንድ ኮፒ ሆኖ ሰነዶቹ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸውና የድርጅቱ ማህተም ያለባቸው መሆን አለባቸው። እንዲሁም ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዕቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል መግለጫ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በግልጽ ከላይ በሚታይ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ብለው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
10. ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ፡- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በ15(አስራ አምስት) ቀናት ከጠዋት 2፡30 እስከ 10፡30 የሥራ መውጫ ባሉት ሰዓቶች ሲሆን ጨረታው የሚዘጋው በቀን ሀሙስ ቀን 29 ሚያዝያ 2018 ከጠዋት 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ሀሙስ ቀን 29 ሚያዝያ 2018 ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል።
11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ስፔስፊኬሽንም ሆነ የዕቃ ዓይነት ከሌለው የለንም ወይም ሰረዝ(~)ማድረግ እንጂ በአማራጭ መሙላት አይችልም።
12. ግሩፑ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን የተሽከርካሪ ዝርዝር ፍላጎት በምስል መቅረብ አለበት ላለበት እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ተጫራቾች ማቅረብ አለባቸው።
13. ግሩፑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ሲፈልጉ:
ስልክ ቁጥር፡– 09 67 26 16 36
ሀይሌ ጋርመንት የቀድም ሪቬራ ሆቴል
አዲስ አባባ
ኢትዮጵያ
መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ግሩፕ