በሀድያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ አስ/ጽ/ቤት ለሚያሰራው የጂ+3 የሴክተር መ/ቤቶች የቢሮ ህንጻ ቀሪ ሥራዎች ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሀድያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ አስ/ጽ/ቤት ለሚያሰራው የጂ+3 የሴክተር መ/ቤቶች የቢሮ ህንጻ ቀሪ ሥራዎች ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 23, 2026)

  የጨረታ ማስታወቂያ

በሀድያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ አስ/ጽ/ቤት ለሚያሰራው የጂ+3 የሴክተር መ/ቤቶች የቢሮ ህንጻ ቀሪ ሥራዎች ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ደረጃቸው BC-5/GC-6 እና ከዚያ በላይ የሆነ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከወረዳው ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 25ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በማስያዝ መግዛት ይችላል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአሠሪው መ/ቤት ስም 250,000 /ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታበማድረግ እንዲሁም አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና የኘሮጀክቱንስም ጠቅሶ የቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሰነዶች አንዲሁም ኦርጂናልቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታበማድረግ አራቱንም የቴከኒካል ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና ሁለቱንምየቴክኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የኘሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጅ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 26ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል። የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል። ኦርጂናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) በየመጠይቁ (ባዶ ቦታዎች) ተሞልቶ ተፈርሞና መሃተም ተደርጎ ታሽጐ መመለስ አለበት። የቴክኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) አለመመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
  4. ጨረታው በ26ኛው ቀን በ5፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። 26ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

ማሳሰበያ፡-

  • የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የመንግሥት የግዢ አፈጻጸም መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል።
  • ማንኛውም ተጫራች ከወቅቱ ገበያ ዋጋ በታች ያቀረበ እንደሆነ አሠሪው መ/ቤት ውል ለመግባት አይገደድም።
  • ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡ 046 263 0265 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በሀድያ ዞን የአንሞ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *