በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የመድሃኒት እና የህክምና መገልገያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የመድሃኒት እና የህክምና መገልገያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 23, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 004/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም /ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ለፌደራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድሀኒቶች እና የሕክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ 53 መድሀኒት ቤቶች የዱቤ /credit እና የጥሬ ገንዘብ/ cash ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው። ስለሆነም ድርጅቱ ከነማ ፋርማሲ የመድሃኒት እና የህክምና መገልገያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

መስፈርቱን የምታሟሉና ብቁ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የቲን ማስረጃዎች።

2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ 7 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ) ጉለሌ /ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ህንጻ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3. ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 430 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ስለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ዳሬክቶሬት ክፍል 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል

ማሳሰቢያ፡ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚዎስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ህንጻ 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403

የስራ ሰአት፡ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 200 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት ከሰዓት 700 ሰዓት እስከ 1100 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 200 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 827-9123

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ስልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *