Addis Zemen (Apr 23, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ ሀይሉ ኢብሳ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ገረመው ኢብሳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/109160 በ16/11/2017 ዓ/ም በመ/ቁጥር/119597 በ25/3/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የቤት ቁጥር 446 የሆነ ቤት የመለያ ቁጥር AA000020400206 የተመዘገበ የተነጻጸሪ ካርታ ያለው የይዞታው ስፋት ጠቅላላ 581.58 ካ/ሜ ሲሆን የቤቱ ስፋት 175 ካ/ሜ ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው በተነጻጻሪ ድርሻ 251 ካ/ሜ በጠቅላላ በፕሮፖርሽን ለቤቱ የሚደርሰው የቦታ ስፋት 426 ካ/ሜ በሐራጅ የሚሸጠው የ7ኛ የፍ/ባለዕዳ የግል ቤቶች ናቸው የተባሉትን 2 ክፍል ቤቶች ሳያካትት ፍርድ ያረፈበትን ቤት ብቻ ሲሆን ገዢው የክ/ተማው መሬት አስተዳደር በመለሰው ምላሽና እስኬች መሰረት የሚረከብ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 16,940,028 (አስራ ስድስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሺህ ሃያ ስምንት ብር) የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ለግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን ፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት