Addis Zemen (Apr 23, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ወዞፋ/ግ/05/2018
የወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱ ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ለመፈጸም ይፈልጋል።
|
ሎት |
የሚገዛው ዕቃ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
ፍራሽ እና ብርድልብስ ግዥ |
50,000 |
|
2 |
የጓሮ አትክልት ዘር ግዥ |
30,000 |
|
3 |
ብርቱካናማ ስኳር ድንች ቁርጥራጭ ግዥ |
40,000 |
|
4 |
የምግብ ዘይት፣ ማካሮኒ እና ፓስታ ግዥ |
40,000 |
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት፣ የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፊኬት፣ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፣የታደሰ የኳራንቲን ሰርተፊኬት (እንደየ ግዥው አይነት የሚጠየቅ ይሆናል) እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም (e-GP) ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ እና የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሀምሳ እያንዳንዱ ሠነድ እየከፈሉ ከወላይታ ዞን ፋ/ፕ/ል/መምሪያ 2ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ 1 ኦሪጅናል እና 1 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለብቻ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል።
4. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
5. አሸናፊ ድርጅት አስፈላጊውን ውለታ በመፈጸም ዕቃውን ሙሉ በሙሉ ወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ድረስ በማቅረብ ገቢ ሲያደርግ ከፍያ የሚፈጸም ይሆናል።
6. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 551 2116 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት
መምሪያ