በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ የተለያዩ VIP ፈርኒቸር ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ የተለያዩ VIP ፈርኒቸር ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 24, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 15/2018

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች በመደበኛ በጀት የተለያዩ VIP ፈርኒቸር ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም

ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር ለመሣተፍ የሚፈልጉ

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው የተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 1130 ሰዓት ድረስ ከግ///አስ/ ዳይሬክቶሬት ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመቅረብ የታደሰ ንግድ ፍቃድ በማሳየት መግዛት አለባቸው።
  3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 11ኛ ቀን ከጠዋቱ 300 – 600 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዝህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን 900 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 11ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  5. ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 9 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በሲፒኦ ወይም አንኮንድሸናል ባንክ ጋራንቲ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው!
  6. ተጫራቾች የጨረታውን በሚወዳደሩ በፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ ከሁለት ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  7. ጨረታው 3 ወራት /90 ቀናት / ብቻ ፀንቶ የሚቆይ የሆናል።
  8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ / በመክፈል ከግ///አስ/ ዳይሬክቶሬት መግኘት ይቻላል።
  9. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሣሰቢያበተጨማሪም ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ

ከቫት ተመዝጋቢዎች ላይ ቫቱን ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን።

ስልክ ቁጥርለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-221-7002/3

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *