2merkato.com (Apr 24, 2026)
የንግድ ቤቶች ኪራይ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ
የግዥ መለያ ቁጥር፡- አአዩ/ብግጨ/የሱቅ ኪራይ/006/2018/26
1. የተጫራጭ ስም————————————————————————————————፡፡
2. የተጫራች አድራሻ……………….አዲስ አበባ……………….ክ/ከተማ………………. ወረዳ…………….የቤት ቁጥር……………. ስልክ ቁጥር……………………………………
3. የንግድ ፈቃድ ቁጥር………………………………………………………………………………
4. ቲን ሰርተፍኬት ቁጥር…………………………………………………………………………….
5. የስራው አይነት……………………………………………………………………………………
6. የሚጫረቱበት ክፍል ቁጥር………………………………………………………………………
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአንድ ካሬ ሜትር ዋጋ ቫትን ጨምሮ…………………………………
ማሳሰቢያ፡-
1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ ፎረም ህንጻ ያሉ ቦታዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች (ለመፃህፍት ቤት፤ ለእስቴሽነሪ እና ለቢሮ አገልግሎት) በግልጽ ጨረታ ለማከራዬት ይፈልጋል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከታች በተገለፀው አድራሻ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ 4፡00 ሰአት ድረስ ጨረታውን ለያዘው ሰው ማሰረከብ ወይም ለዚህ ጨረታ በዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡30 ሰአት ይከፈታል::
3. ከዚህ የጨረታ ሰነድ ጋር የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ቲን ሰርተፍኬት መያያዝ አለበት፡፡
4. የጨረታ አሸናፊዎች የኪራይ ውል መዋዋል የሚችሉት ለጨረታ ባስገቡት የንግድ ፈቃድ ስም ብቻ ነው፡፡
5. በጨረታ ያሸነፉበትን ክፍል በምንም ዓይነት ለሌላ ወገን ስም ማዞርም ሆነ ተከራይቶ ማከራየት የማይቻል ሲሆን ይህንን ለማድረግ የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ እና የኪራይ ውሉ እንደሚሰረዝ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
6. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በተገላፀው አድራሻ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ ይዘው በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ይህ የጨረታ መጋበዣ ሰነድ የሚያካትታቸው ዋና የሚከራዩ ቦታዎች ዝርዝር እና የሚከራይ ቦታውን የሚያሳይ ዲዛይን ይሆናል፡፡
9. ይህ የኪራይ አገልግሎት ጨረታ ታሳቢ የሚያደርገው በአገር ውስጥ ለሚፈፀም የአገልግሎት ሽያጭ (የምክር አገልግሎት አይጨምርም) የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይሆናል፡፡
10. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6ኪሎ ዋናው ግቢ የአስተዳደር ህንፃ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 314 ስልክ ቁጥር 251+111243290
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ