የሲር ለና በጎ አድራጎት ድርጅት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሲር ለና በጎ አድራጎት ድርጅት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 24, 2026)

መኪና ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ለየሲር ለና በጎ አድራጎት ድርጅት በኢትዮጵያ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በምዝገባ ቁጥር 4979 ተመዝግቦ በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ወላጅ አጥ ህጻናት ተኮር የሆኑ የልማት እና የሰብአዊ ድጋፍ ዙሪያ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን የራሱን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ በጽ/ቤቱ ለሚሰጠው አገልግሎት እና የሰብአዊ ድጋፍ ስራ የሚውል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም

  1. በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያለው
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
  3. ክፍያ እንደተፈጸመ ወዲያውኑ መኪናውን ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን/የመኪናውን ስፔሲፊኬሽን ከድርጅቱ ዋና /ቤት መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ከተጫረቱበት ዋጋ በላይ ዋጋ መጨመር አይችሉም።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በተሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በሚታሰብ 5 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

 ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡አዲስ አበባ ጉለሌ /ከተማ ወረዳ 09 ጳውሎስ ሆስፒታል ጀርባ ኢትዮፓረንትስ /ቤት አጠገብ።

ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ስልክ ቁጥር፡-09-12-49-00-06 / 09 78 99-99-59

የሲር ለ በጎ አድራጎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *