Addis Zemen (Apr 24, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EU/Dist./NCB-009/2018
ተቋማችን የተለያዩ መጠን ያላቸው ጥሬ እንጨት ምሰሶዎችን በሚያቀርበው ቁርጥ ዋጋ መሠረት ለማቅረብ ፍቃደኛ ከሆኑ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት |
የጥሬ እንጨት ምሰሶ የሚቀርብበት |
የምሰሶ አይነት |
ብዛት በቁጥር |
|
1 |
ባህር ዳር |
ከባለ8-12 ሜትር |
2,000 |
|
2 |
ነቀምት |
ከባለ8-12 ሜትር |
6,000 |
|
3 |
ሻሸመኔ |
ከባለ8-12 ሜትር |
2,000 |
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ አሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ክሊሪንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫሪቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 10ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ዲሰትሪቢውሽን ግዥ ክፍል በመምጣት የጨረታ ዶክመንቱን ሶፍት ኮፒ በነጻ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላለ።
3. አድራሻ፡– ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ላይ ዲስትሪቢውሽን ግዥ ከፍል ስልክ ቁጥር 011-1266605
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ በተጠቀሰው ቀን፤ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
5. ጨረታው ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
6. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት