የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአጥር ሥራ፣ አደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ እድሳት፣ ኢንሲነሬተር ጥገና እና የምግብ ማብሰያ ብሎክ እድሳት ስራ ለማስገንባት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአጥር ሥራ፣ አደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ እድሳት፣ ኢንሲነሬተር ጥገና እና የምግብ ማብሰያ ብሎክ እድሳት ስራ ለማስገንባት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 24, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 2018 በጀት ዓመት በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ የአጥር ሥራ፣አደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ እድሳት፣ኢንሲነሬተር ጥገና እና የምግብ ማብሰያ ብሎክ እድሳት ስራ ለማስገንባት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡

  • በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ደረጃ 6 BC /GC እና ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸዉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ ፡፡
  • የግዥ መጠኑ 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  • ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናሉን በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፣
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአጥር ስራ፣አደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ እድሳት፣ኢንሲነሬተር ጥገና እና የምግብ ማብሰያ ብሎክ እድሳት ስራ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
  • ተጫራቾች የሚሳተፉባቸውን ጨረታዎች በሆስፒታሉ የጨረታ ሰነድ አይነትና ዝርዝር / ስፔስፊኬሽን/ መሰረት ሰርተው ማስረከብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የአጥር ስራ፣አደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ እድሳት፣ኢንሲነሬተር ጥገና እና የምግብ ማብሰያ ብሎክ እድሳት ስራ የሚያስፈልጉ እቃዎችን ሙሉ በሙሉ በራሳቸዉ ማቅረብና ሰርተው ማስረከብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ለሚሳተፉበት ጨረታ ህጋዊ ተቀባይነት እና አግባብነት ያለዉ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸዉ።
  • ተጫራቾች በቀረበው ጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ የቀረቡትን ስራዎች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት አለባቸው ፡፡ነጣጥሎ መሙላት አይቻልም።
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን የአጥር ስራ፣አደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ እድሳት፣ኢንሲነሬተር ጥገና እና የምግብ ማብሰያ ብሎክ እድሳት ስራ በሆስፒታሉ የጨረታ ሰነድ ስራ ዝርዝር መሰረት ሰርተዉ ማስረከብ አለባቸዉ ፡፡ የስራ ጥራት ችግር ቢከሰት በራሳቸዉ ወጭ እንደገና የመስራት ግዴታ አለባቸዉ።
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን ግንባታ ትክክለኛነቱ ሆስፒታሉ በሚመለከታቸው ባለሞያዎችና ሃላፊዎች በማረጋገጥ ይረከባል፡፡
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን የአጥር ስራ፣አደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ እድሳት፣ኢንሲነሬተር ጥገና እና የምግብ ማብሰያ ብሎክ እድሳት ስራ እቃ አቅርቦት ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት ፡፡ የጥራት መጓደል ቢኖር በራሳቸዉ ወጭ የማስተካከል ወይም የመተካት እና የመስራት ግዴታ አለባቸው።
  • ጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ወይም ቢድቦንድ/ 1% እና ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ፣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው፡፡ተጫራጮች በጨረታው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ወይም ተቋራጭ ዝርዝር የግንባታ ዋጋ /cost Break down እና የግንባታ መርሃ ግብር/Project work schedule/ እንዲሁም ባቀረበው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ/Conformation letter/ አሸናፊነቱ በተገለፀ 5 የስራ ቀናት ውስጥ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህን ማድረግ ካልቻለ ከውድድር ውጭ ሆኖ ሁለተኛው የወጣው ተጫራች የሞላው ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ሲነፃፀር የተሻለ ሆኖ ከተገኘ ስራው ለዚሁ ተወዳዳሪ የሚሰጥ ይሆናል።
  • የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ሞልተው አሸናፊ ሆነው የሚመረጡ የግንባታ ተቋራጮች ውል ይዘው ወደ ስራ ሲገቡ ቅድመ ክፍያ አይፈቅድላቸውም።
  • አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ስራ አሸናፊነቱ በተገለፀበት 5 አምስት ቀን ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ በውልና ማስረጃ ውል በመፈፀም ስራውን መጀመር አለባቸዉ።
  • የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ አቅርቦ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ፣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ21 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 22ኛዉ ቀን 400 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ 400 ይታሸጋል፡፡ 22ኛዉ ቀን ከቀኑ 430ሰዓት ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን በዓላት ቀን ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
  • የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ 6 ቀን ፀንቶ ይቆያል።
  • ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ //አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት፣ በስልክ ቁጥር 0116813390 ወይም በፋክስ 0116811008  ቁጥር በመላክ መጠየቅ ይቻላል።
  • /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *