Addis Zemen (Apr 24, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ሰኢድ አህመድ ኑር እና የፍ/ባለዕዳ ብሉናይል ጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ሥራዎች አክሲዮን ማኅበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 335823 በ30/10/2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/344562 በ18/05/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት በብሉናይል ጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ሥራዎች አክሲዮን ማኅበር ስም የተመዘገበ በካርታ ቁጥር የካ/239771/13 በሰሪያል ቁጥር 0161894 የቦታው ስፋት 3,435 ካ/ሜ የቤቱ አገልግሎት ለድርጅት የሆነ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የሚገኝ በአሁኑ ጊዜ ጅምር ቤትና አንድ ወለል ሥራ የተከናወነ ግንባታ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 272,145,376.75 (ሁለት መቶ ሰባ ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ አርባ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ስድስት ከ75/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ በግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት