Addis Zemen (Apr 24, 2026)
በድጋሚ የወጣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዢ የጨረታ ማስታወቂያ
1. የተቋሙ ስም ፡– ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ
2. አድራሻ ፡– ወላይታ ሶዶ ከተማ
3. የጨረታ ዓይነት ፡– ግልፅ ጨረታ
4. የጨረታ ማጣቀሻ ቁጥር 006
5. ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች
- ሎት1. ኤሌክትሮኒክስ
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው
1. በዘመኑ ተጫራቾች ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በሀገሪቱና በክልሉ የግብር ሕጎች በተደነገገው መሠረት የግብርና የታክስ ግዴታቸውን የተወጡ፤
2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 3% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ስም አዘጋጅተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ዋናውን እና ኮፒውን ስልጣን ባለው አካል ተፈርሞና ማህተም ተደርጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል፡፡ሆኖም 16ተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች ወይም ወኪሎች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ማካተት አለማካተቱን መግለጽ ይኖርባቸዋል፤ ሆኖም ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ስለማካተት አላማካተቱ በግልጽ ያላመለከቱ ከሆነ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
8. ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴከኒክ መገምገሚያ መስፈርቶችን በመሙላትና በተለያዩ አራት ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የፋይናንስ ኦሪጂናል እንዲሁም ኮፒ የቴክኒክ ክብር ፣ ኦሪጂናል እንዲሁም ኮፒ መሆኑን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. አሸናፊ ድርጅቶች እንደ አስፈላጊነቱ ውል ከመውሰዳቸው በፊት መ/ቤቱ የጠየቀውን የዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
10. ተጫራቾች የሚሞሉት የዕቃ ዋጋ ላይ መለኪያና ጥራቱን ጠብቀው መሙላትና ማቅረብ አለባቸው።
11. በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ታግዶ የነበረ ከሆነ የዕገዳ ግዜውን ያጠናቀቀ።
12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከወጣው ጨረታ ውስጥ ከብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ) እና ከዚያ በላይ ዋጋ ባለው ግዥ የሚሳተፍ ማንኛውም የሀገር ውስጥ ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
13. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾ በሚሰጠው የዕቃ ግዥ ትዕዛዝ መሰረት ዕቃዎቹን በራሱ ወጪ አስከ መ/ቤቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት የማስረከብ ግዴታ አለበት።
14. ውል የሚፈጽም ማንኛውም ሰው ውል ለመፈፀም የሚያስችል የሕግ ችሎታ ያለው መሆን ይኖርበታል።
15. በዕዳ ያልተያዘ፣ያልከሠረ ወይም የሥራ እንቅስቃሴውን ያላቋረጠ፣የንግድ ሥራ እንቅስቃሴው ያልታገደ፣ወይም በዕነዚህ ምክንያቶች ተከሶ በክርክር ላይ ያልሆነ።
16. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በፅሁፍ ከተገለፀለት በኃላ ባሉት 7 ቀናት ውስጥ ውለታውን በመውሰድ ውል መፈራረም አለበት፡፡ ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይገባ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይደረጋል።
17. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ማብራሪያ ከፈለጉ በቢሮው የግዥና/ፋይ/ንብ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7 በአካል በመምጣት 7 ወይም በስልክ ቁጥር 046-180-5841 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ