Addis Zemen (Apr 25, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ፡ 008/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡–
- ሎት አንድ – የሰራተኞች ክበብ ካፍቴሪያ (የካፌቴሪያ የመስሪያ ቦታ፣ ውሀ እና መብራት ነጻ ሆኖ ክፍያ የማይፈጸምባቸው ሲሆን ወጪው በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሚሸፈን ይሆናል።
- በተጨማሪም ተጫራቹ ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ሙሉ ቁሳቁሶችን እና የካፍቴሪያ መገልገያ ዕቃዎች አሟልቶ መግባት የሚችል መሆን ይኖርበታል).
- ሎት ሁለት – የማዕድን ውሃ
- ሎት ሶስት – ቆሎ
- ሎት አራት – ለካፍቴሪያ የሚሆን ወንበርና ጠረጴዛ
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈስጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከማይመለከታቸው (ከሎት 3) ውጪ ያሉ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴከኒክ ፕሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮፒ እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል ኮፒ” የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ በኤንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የስራ ቀን) በ4፡00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ 50,000.00 ፣ ለሎት ሁለት 10,000፤ ለሎት ሶስት 10,000 እንዲሁም ለሎት አራት 10,000 ብር በሚወዳደሩበት ሎት በባንክ በተመሰከረለት ቼክ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው። CPO መሰራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚል አድራሻ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 11፡00 ሰዓት ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከማይመከለታቸው (ከሎት 3) ውጪ ያሉ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ/ቫት/ ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ/ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል። ያልተገለፁ ከሆነ ተ.እ.ታ/ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም እቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስገባት አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 011 557 5742/ 011 557 5719 በመደወል ወይንም ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ