Addis Zemen (Apr 25, 2026)
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መ/በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስ/ር የመጀ/ደ/ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆን ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁም መሰረት፡–
- በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በዕቃ አገልግሎት አቅራቢነት የተመዘገበ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ(Specification) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 15(አስራ አምስት) ተከታታይ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት በሚ/አ/ከ/አስ/ር የመጀ/ደ/ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ን/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ(CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን ሞልተው የሚያቀርቡት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተቀመጠው የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎት የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በሚለው የዕቃዎች ዝርዝር መሰረት ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም አርፎበትና ተፈርሞበት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀኖች ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ተኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጣለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ስነ–ስርዓቱን አያስተጓጉልም።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታውን ያሸነፈ ያሸነፋቸውን ዕቃ ለሚ/አ/ከተ/አስ/ር የመ/ደ/ፍ/ቤት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 28 28 76 98 እና 09 17 15 17 12 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መ በቤንች ሸኮ ዞን
የሚዛን አማን ከተማ አስ/ር የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት