Addis Zemen (Apr 25, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር የንግድ ቤት ኪራይ 08/2018
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት የካፒታል እቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የስራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን በአራዳ ክ/ከተማ ከጊወርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን የሚገኘዉ የኩባንያዉ ዋና መ/ቤት ህንጻ ዉስጥ ቤዝመንት 1 ለመኪና ፓርኪንግ አገልግሎትና እና 9ኛ ፎቅ ለGY አገልግሎቶች ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ጋብዘናል።
1. ተጫራቾች ተወዳድረዉ ባሸነፉበት ቤት ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ለማውጣት፣ ቤቱን ተከትሎ የተጠቀሙበትን የዉሀ እና የመብራት ፍጆታ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለቤዝመንት 1 ለመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር) እንዲሁም 9ኛ ፎቅ ለGY አገልግሎት 5000 (አምስት ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 3/2018 ዓ.ም የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን በሚገኘው አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ፣ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላለ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ፋይናሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ግንቦት 3/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በቀን 3/9/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኢማ 4ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።
6. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድረሻ፡- ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 44 34 72 13 ደውስው መጠየቅ ይችላሉ።
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ