Addis Zemen (Apr 25, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 12/2018
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለሠቁ ኢት 4-21646 ቶዮታ ሃይላከስ ደብል ጋቢና አገልግሎት የሚውል ጥገና ማለትም የአካል ጥገና ቀለም ቅብ፣ የኤሌክትሪክ ስርዓትን ፈትሾ መጠገን፤ የሲሊንደር ሄድ ከዳን ሲል መጠገን እና የፊት እግር ሰርቪስ ማድረግ እና የራዲያተር መደጊያ ፓኔል የላይኛው እንዲሁም የሚቀየሩ ፓርቶች: የመኪና አካል በሺንግ፣ የበር ዙሪያ ጎሚኒ፣ የበር ምስለነሚኒ፣ የኋላ በር የመስታወት ዘንግ፣ ግራና ቀኝ ጭቃ መከላከያ ተንጠልጣይ አራቱም፣ የኋላ ፓራውልት ተለጣፊ ፕላስቲክ፣ የኋላ ሰሌዳ መለጠፍያ መደብ፣ የአራቱም በር የመስታወት የውጭ ካናል (ዘንግ)፣ የሰስፔንሽን ቡሺንግ፣ የመሪ ፓምፕ፣ የዝናብ መጥረጊያ፣ የመብራት አምፖሎች፣ የጋቢና አየር ማጣሪያ፣ የካም ሻፍት ዘይት ሲል፣ የፊትና የኋላ ዲፈረንሻል ዘይት ሲል፣ የፍሬን ላይኒንግ፣ የመሪ ዘንግ፣ የበር መዝጊያ ቁልፍ የኋላና የፊት በር እና የግራና ቀኝ በኩል ፊንደሮች ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቸቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ላላቸው ግዢዎች የቫት ተመዝጋቢ ሥለመሆናቸው ማስረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡመሆናቸው የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግስት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፍል ከባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት የግ/ን/አስ/ኬዝ ቲም የቢሮ ቁጥር መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ሰላሳ/30/ ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ነው።
- አቅራቢዎች ጨረታውን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው መሠረት አቅራቢው በፈለገው በአንዱ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ወጭ በኢንሹራንስ ዋስትና መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል።
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለልጣን
ግ/ን/አስ/ኬዝ ቲምት
የፖስታ ሳጥን ቁጥር 404
ስልክ ቁጥር 046-131 5008/ 09 23 69 00 85
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን