አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Apr 26, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከተዉን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም .. በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡

የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.. ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት .. ወዲያዉ ይመለስላቸዋል።

ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።

የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።

ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል፡፡

በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።

የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ /ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ ኢማ ዋና መስሪያ ቤት 4 ፎቅ ላይ በሚገኘው የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-515-1153 እና 0115 15 07 11 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የመያዣ

ሰጪው

ስም

የንብረቱ

አይነት እና

አገልግሎት

የቦታው ስፋት በካ.

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ

ቁጥር

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታ መነሻ

ዋጋ በብር

ጨረታው

የሚካሄድበት ቀን

 

የምዝገባ ሰዓት

 

የጨረታ ሰዓት

 

ጨረታው የወጣበት ጊዜ

 

1

ኣቶ አላዬ ጋሼ

አይናለም

ተበዳሪዉ

G+1 የመኖሪያ ቤት

 

175

 

AA000090600982

 

አዲስ አበባ ከተማ

ኮልፌ ቀራንዮ /ከተማ

26,325,726.00

ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም

 

4:30-5:30

5:30-6:00

 

በድጋሚ

2

አቶ ተማም ዘይኑ ሁሴን

 

ተበዳሪዉ

የመኖሪያ ቤት

63.44 (ከአጠቃላይይዞታው ላይ 373% ወደፊት ለመንገድ ማስፋፊያ የሚቀነስ)

የምስክር ወረቀት ቁጥር

ETH000100000000004254469

የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር

AA000090707791

 

አዲስ አበባ ከተማ

ኮልፌ ቀራንዮ /ከተማ

ወረዳ 07

5,629,085.86

ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም

 

8:30-9:30

9:30-10:00

 

ለመጀመሪያ

ጊዜ

 

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *